Jems ethio commando) በኢትዮጵያ አቆጣጠር መስከረም 12 ቀን 1996 ዓ.ም በጅማ ዞን፣ ሰቃ ወረዳ ተወለደ። እናቱ ወይዘሮ አይሻ ሼክ መሐሙድ፣ አባቱ አባጅሃድ ይበላሉ። ሙሐመድ ለቤተሰቡ የመጨረሻ ልጅ በመሆኑ፣ እንደ ዕድሜውእንደ እኩዮች ተጫውቶና ተዝናንቶ የማሳለፍ እድል አላገኘም። የቤቱ አጠቃላይ ኃላፊነትና ስራዎች በሙሉ በእሱ ትከሻ ላይ የወደቁ ነበሩ።በ2003 ዓ.ም ገና በልጅነቱ የቁርዓን ትምህርት መቅራት ጀመረ። ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስም ጎን ለጎን ዘመናዊ ትምህርቱን መከታተል ጀመረ። ነገር ግን ቁርዓን የሚቀራበት ቦታ እጅግ ሩቅ በመሆኑ እና በቤት ውስጥ የነበረበት ኃላፊነት ከባድ ስለነበር፣ ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ግዴታ ሆነበት። ከጓደኞቹ ወደኋላ ላለመቅረት በማሰብ ትምህርቱን ለመቀጠል ወሰነ።በትምህርቱ በጣም ጎበዝ ቢሆንም፣ በወላጆቹ መካከል ይፈጠር የነበረው የእርስ በእርስ ግጭት እና እሱን መፈታት አለመቻሉ በውስጡ ትልቅ ንዴትና እጫጫት ይፈጥርበት ነበር። በመጨረሻም ከቤተሰቡ ርቆ ለመኖር በመወሰን ወደ ጅማ ዞን አቅናቶ ስራ መፈለግና መስራት ጀመረ።2. የትግል፣ የሙያ እና የትምህርት ጉዞከሁለት ዓመት የራቀ ህይወት በኋላ እናቱን በጣም በመናፈቁ ወደ ቤተሰቦቹ ተመለሰ። እናቱን እያገዘ ትምህርቱን ለመቀጠል ቢሞክርም፣ በወላጆቹ መካከል ያለው ችግር አለመቀየሩን ሲረዳ እስከመጨረሻው ራሱን ችሎ ለመቆም ሁለተኛ የማያዳግም ውሳኔ ወሰነ።እንደገና ወደ ጅማ ዞን በመመለስ በሙስሊም ምግብ ቤት ውስጥ ስራ ጀመረ። ሙሐመድ በስራው እጅግ ጠንካራ፣ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር የሚጓጓ እና የድካም ስሜት የማይታይበት ልጅ ነበር። ከቀጣሪዎቹም ሆነ ከደንበኞች ጋር መልካም ግንኙነት ነበረው
ከ2008 እስከ 2010 ዓ.ም በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ ከቆየ በኋላ፣ ህይወቱንና ታሪኩን መቀየር እንዳለበት ተገነዘበ። ቦታውን በመቀየር በሼፍነት (በምግብ ዝግጅት ሙያ) እየሰራ፣ ከሚያገኘው ደመወዝ እራሱን አስተምሮ ትምህርቱን ቀጠለ። ከዚያም አልፎ በራሱ ወጪ የስፖርት ክለብ በመመዝገብ ለ3 ዓመታት ያህል ትምህርቱን፣ ስራውን እና ስፖርቱን ጎን ለጎን በትጋት አስኬደ። የሰዎች አክብሮትና ፍቅርም ለተጨማሪ ስኬት መንፈስ አበራታው
ራሱን ችሎ የራሱን ንግድ መስራት ከጀመረ በኋላ፣ በውስጡ ድብቅ የነበረው ትልቅ ህልም - ወታደር የመሆን ፍላጎት አሸነፈው።ወዲያውኑ ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመመዝገብ የስልጠና እድል አገኘ። የስልጠናው ሁኔታ እሱ ከጠበቀው በላይ እጅግ ከባድ፣ ፈታኝ፣ የአየር ጠባይ መለወጥና ጥብቅ ወታደራዊ ህጎች የበዙበት ቢሆንም፣ ለምንም አይነት ፈተና እጅ ሳይሰጥ በስኬት ተመረቀ።በኋላም ለየት ለምለምልው እና እጅግ ከባድ ለሆነው የኮማንዶ ስልጠና ተመረጠ። የኮማንዶ ስልጠና ከየትኛውም ስልጠና በላይ፡ጥንካሬን፣አስተዋይነትን፣መረጋጋትን እና ጀግንነትን የሚጠይቅ፣ በአንድ ትንሽ ስህተት ህይወት ሊያልፍባት የሚችልበት ከባድ መንገድ ነበር።ሙሐመድ ጀማል እነዚህን ፈተናዎች በሙሉ በፅናትና በብቃት በማጠናቀቅ የኮማንዶነት ማዕረጉን የተቀናጀ ሲሆን፣ ዛሬ ላይ "Jems ethio commando" በመባል ለብዙዎች የፅናት፣ የጽኑ እምነት እና የጠንካራ ስራ አርአያ ለመሆን በቅተዋል
ወደ ስራውም ስገባ ስራዎቹ ሁሉም ከባድ ነበሩ በጣም ጽናትን የሚጠይቁ አካላዊ ጥንካሬና የአይምሮ ብስለትን የአላማትጽናት የምጠይቁ የራስን ፍላጎት ሁሉንም ገለው ለህዝብ መኖር ለህዝብ ዋጋ መክፈል ግዴታ እንደሆነ የሰለጠነውን በተግባር ማሳየት ጀመረ ሙሃመድጀማል በኢትዮጵያ በብዙ ቦታዎች ግዳጅ ፈፅመዋል ይሁን እንጂ ያሰለፋቸው ነገሮች አንዳንዴ ቆም ብሎ ሲያስብ
ምንም ነገር ማድረግ እንደምቻል አረጋግጠው ይናገራል ከዛም በ 20017 ዓመት ከዚህ በፊት የተለያዩ ትርዒቶች ላይ ስለነበረ በፀባይም በአካላዊ እንቅስቃሴ የተሻለ ስለነበረ የአሰልጣኝነት እድል ጠራቸው አሰልጣኝ ሆነው የመጀመሪያውን የአሰልጣኝነት መመጣጠን እንደጨረሰ የመጀመሪያ ዙር የህዳሴ ኮርስ በፌዴራል የመጀመሪያው አይበረው ጀግና ወተሮችን ማፍራት ችለዋ በ 20018 ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ ልዩ ተልዕኮ ተሰጠው እሱም ኢትዮጵያውያኖችን ወከለው ከሀገር ወተው ዱባይ ላይ የስዋት ቻሌንጅ ላይ እንድስሳተፍ ተጋበዜ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ተጠቅመው ምንም አይነት ስህተቶች በሱ ምክንያት ሰይፈጠሩ ግዳጁን ጨርሰው ወደ አሀዱ ታቀላቀለ ሙሃመድ በዚህ ቆይታ ውስጥ አንድ ሁሌም ከአንደበቱ የማይጠፋ ቃል አለ እሱም ይቻላል የምለው ቃል🙏
ጀምስ ይቻላል የምለዉን ቃል
ወደተግባር ለውጦአሳይቶናል.